ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደዚህ ኡመት መጀመሪያ እስኪደርስ ድረስ ከቀደምት ነቢያት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወራረሱትና በመካከላቸው ሲቀባበሉት ከነበሩ አደራዎች መካከል ልትሰራው የምትፈልገውን ስራ ተመልከት! ማድረጉ የማያሳፍር ስራ ከሆነ ስራው! የሚያሳፍር ስራ ከሆነ ተወው! የሚለው ይገኝበታል። ፀያፍን ከመስራት የሚከለክለው ሀፍረት ነው። ሀፍረት የሌለው ሰው በየትኛውም ፀያፍና ውግዝ ተግባር ውስጥ ይዘፈቃል።