explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድን ሰውዬ ለወንድሙ አይነአፋርነት ማብዛት እንዲተው ሲመክረው ሰሙትና አይነአፋርነት ከኢማን መሆኑን እና ከመልካም በስተቀር ይዞ እንደማይመጣ ገለፁለት። አይነአፋርነት መልካም ድርጊት ለመስራትና እኩይ ተግባር ለመተው የሚያነሳሳ ስነምግባር ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከመልካም ተግባር የሚከለክል ባህሪ ተወዛጋቢነት፣ ደካማነት፣ ልፍስፍስነትና ፈሪነት እንጂ አይነአፋርነት አይባልም።
  • ከአሏህ ሓያእ ማድረግ የሚሆነው ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላትን በመተው ነው።
  • ከፍጡራን ሐያእ ማድረግ የሚሆነው እነሱን በማክበር፣ በሚመጥናቸው ደረጃቸው ላይ በማስቀመጥና በተለምዶ ከሚያፀይፍ ድርጊት በመራቅ ነው።