explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው በዲናዊ፣ በዱንያዊ፣ ለራሱ በሚሰራቸው፣ ከሌሎች ጋርም ባለው ጉዳዮች ለስላሳነትን ያልተገጠመ (ያልታደለ) ሰው በርግጥም መልካምን ሁሉ እንደተነፈገ ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የለስላሳነት ትሩፋትን፣ እርሱን በመላበስ መነሳሳቱንና ድርቅና መወገዙን እንረዳለን።
  • በለስላሳነት የሁለቱም ሀገር ስርአት መስተካከልና የሁለቱም ሀገር ጉዳዮች መቅለል ሲገኝ በድርቅና ግን የዚህ ተቃራኒ ነው የሚገኘው።
  • ለስላሳነት ከመልካም ስነምግባርና ከሰላማዊነት የሚመነጭ ሲሆን ድርቅና ደግሞ ከቁጡነትና ከመጥፎ ስነምግባር የሚመነጭ ነው። ለዚህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለስላሳነትን አወደሱም እጅግም አሞካሹት።
  • ሱፍያን አሥሠውሪይ አላህ ይዘንላቸውና ለባልደረቦቻቸው "ለስላሳነት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" አሉ። ቀጥለውም "እርሱም ሁሉንም በቦታቸው ማስቀመጥ ነው። ብርቱነትን በቦታው፣ ልስላሴን በቦታው፣ ሰይፍን በቦታው፣ አለንጋን በቦታው ማስቀመጥ ነው።" አሉ።