ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ እና በሚመለስበትና በስራው የሚመነዳበት በሆነው በመጨረሻው ቀን ያመነ ባሪያ ኢማኑ እነዚህን ጉዳዮችን በመፈፀም ላይ እንደሚያነሳሳው ገለፁ: የመጀመሪያው: መልካም መናገር ነው። በዚህ ውስጥ ሱብሓነላህ ማለት፣ ላኢላሃኢለላህ ማለት፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ በተጣሉ ሰዎች መካከል ማስማማት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ይህንን ካልፈፀመ ዝምታን ያዘውትር፣ ክፋቱን ይቆጥብ፣ ምላሱን ይጠብቅ። ሁለተኛ: ጉረቤትን ማክበር፡ ይህም እነሱን ባለማወክና ለነርሱ በጎ በማድረግ ነው። ሶስተኛ: ለመዘየር የመጣን እንግዳ መልካም በማናገር፣ ምግብ በማብላትና ይህን በመሳሰሉት ማክበር ነው።