ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በንግግርም ይሁን በተግባር ገራገርነት፣ ለስላሳነትና እርጋታ ነገሮች ላይ ውበት፣ ምሉዕነትና ማማር የሚጨምሩ ሲሆኑ እንዲሁም ይህንኑ ባህሪ የተላበሰ ሰውም ፍላጎቱን ለማሳካት የተገባ እንደሆነ ገለፁ። ገራገር (ለስላሳ) አለመሆን ደግሞ ነገሮችን ያነውራቸዋልም አስቀያሚ ያደርጋቸዋልም፤ ስለዚህም ባለቤቱ አላማውን እንዳያገኝ ይከለክለዋል። ካገኘም በችግር ነው የሚያገኘው።