ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ በኛ ላይ በሁሉም ነገሮች ኢሕሳንን ግዴታ እንዳደረገ ተናገሩ። ማሳመር (ኢሕሳን) ማለት በአምልኮውም ውስጥ፣ መልካምን ሲፈፅምም፣ ከፍጡራን ላይ ጎጂን ነገር ሲያስወግድም ዘውትር አላህ ያየኛል ማለት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በመግደልና በማረድ ውስጥ ማሳመርም አንዱ ነው። በመግደል ኢሕሳን ሲባል በቂሷስ (ሸሪዐዊ የቅጣት ብይን ለምሳሌ የገደለ መገደል) ተፈፃሚነት ወቅት: ለመግደል ገሩን፣ ቀላሉንና የተገዳዩን ነፍስ በፍጥነት ሊያወጣ የሚችለውን መንገድ በመምረጥ ነው። በእርድ ማሳመር ሲባል ደግሞ እንስሳ በምናርድበት ወቅት ነው። ይህም መሳሪያውን በደንብ በመሞረድ ፣ የሚታረደው እንስሳ እያየ ፊት ለፊቱ ባለመሞረድና ሌላ እርዱን የሚመለከት እንስሳ ቦታው ላይ እያለ ባለማረድ ለእንስሳ በማዘን ነው።