explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ አንዳንድ ባሮቹን እንደሚወድ ገለፁ። ከነርሱም መካከል ፈሪሃ አላህ የሆነ አንዱ ነው። እርሱም:- የአላህን ትእዛዛት የሚተገብርና ክልከላዎቹን የሚርቅ ነው። ከሰዎች የተብቃቃንም ይወዳል። እርሱም:- በአላህ በመመካቱ የተነሳ ከሰዎች የተብቃቃና ከአላህ ውጪ ወደ ማንም የማይዞር ነው። ድብቅንም ይወዳል። እርሱም:- ለጌታው ባሪያና የሚተናነስ፣ በሚጠቅመው ነገር ላይ የሚጠመድ፣ ማንም እርሱን ማወቁም ይሁን ስለርሱ በሙገሳና ውዳሴ ማውራቱን ከቁብ የማይቆጥር ሰው ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አላህ ባሮቹን እንዲወድ የሚያስፈርዱ አንዳንድ ባህሪያቶች መገለፃቸውን እንረዳለን። እነርሱም:- አላህን መፍራት፣ መተናነስና አላህ የሰጠንን ወደን መቀበል ነው።