ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: ዱንያ ውስጥ ወደኔ ተወዳጁ፤ የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሆነው ስነምግባሩ ያማረ ነው። ዱንያ ውስጥ ወደኔ የተጠላው የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ከኔ የራቀው መጥፎ ስነምግባር ያለው፤ (ሠርሣሮች) ከእውነት ለመውጣት ከአቅሙ በላይ እየተጣጣረ ንግግር የሚያበዛ፤ (ሙተሸዲቆች) ያለምንም ጥንቃቄ አንደበተ ርቱዕ ለመባልና ንግግሩን ለማላቅ ንግግሩን የሚያሰፋ፤ እና (ሙተፈይሂቆች) ናቸው። ሶሐቦችም የአላህ መልክተኛ ሆይ! "ሠርሣሮች" እና "ሙተሸዲቆች"ን አውቀናል። "ሙተፈይሄቆች" ማን ናቸው? አሉ። እርሳቸውም: "ኩራተኞች፣ ንግግራቸውን በማስፋትና በንግግራቸው አፋቸውን በመክፈት በሰዎች ላይ የሚያፌዙ ናቸው።" አሉ።