የአማኞች እናት የሆነችው ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ በማለት ተናገረች: ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት እነርሱን ይዛ የሚበላ ነገር እንድትሰጣት ልትለምናት መጣች። ዓኢሻም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስትሰጣት ለራሷ ምንም ሳትበላ ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ ሲገቡ ሁኔታውን ነገረቻቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ያደረገ፣ በስነስርዓት ያነፃቸው፣ ያለበሳቸውና በዚህም ላይ የታገሰ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።"