explain-icon

ትንታኔ

ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መካከል ፀያፍ መናገር ወይም ፀያፍ ድርጊት አይገኝም ነበር። ትዝም አይላቸው። እሳቸው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የላቀ ስነምግባር ባለቤት ነበሩ። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ዘንድ ከናንተ መካከል በላጩ መልካምን በመለገስ፣ ፊቱን በመፍታት፣ ሰውን ከማወክ በመቆጠብና የነሱን ክፋት በመቻል እንዲሁም ሰዎች ጋር ባማረ መልኩ በመኗኗር ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።"

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አንድ አማኝ ከፀያፍ ንግግርና ከመጥፎ ተግባር ሊርቅ እንደሚገባው እንረዳለን።
  • የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ምሉዕ መሆኑንና ከሳቸው መልካም ስራና ምርጥ ንግግር እንጂ ሌላ እንደማይመነጭ እንረዳለን።
  • መልካም ስነምግባር የሽቅድድም መድረክ መሆኑን እንረዳለን። የቀደመም ምርጥ አማኝና ኢማኑ የሞላ ይሆናል።