explain-icon

ትንታኔ

መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው ቀኑን በመፆምና ሌሊቱን በመቆም የዘወተረ ሰውን ደረጃ እንደሚደርስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ። መልካም ስነምግባር ሲጠቀለል: መልካምን መለገስ፣ ንግግርን ማሳመር፣ ፊትን መፍታት፣ ሰውን ከመጉዳት መቆጠብና የነሱን ክፋት መቻል ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ኢስላም ስነምግባርን በማጥራትና በማሟላት ላይ ትልቅ ትኩረት መቸሩን እንረዳለን።
  • አንድ ሰው በመልካም ስነምግባሩ ቀን ምንም ሳያፈጥር የሚፆምና ምንም ሳይደክም ሌሊቱን የሚቆም ሰው ደረጃ ላይ መድረሱ የመልካም ስነምግባርን ትሩፋት ያስረዳናል።
  • ቀኑን መፆምና ሌሊቱን መቆም ለነፍስ የሚከብዱ ትልልቅ ስራዎች ናቸው። መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው የነርሱን ደረጃ የደረሰው ነፍሱን በመልካም መስተጋብር ላይ ስለታገለ ነው።