ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነፍሱ የሚወደውን አምልኮዎችና ሃይማኖታዊም ይሁን ዱንያዊ መልካም ነገሮችን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ፤ ለነፍሱ የሚጠላውንም ለርሱ እስኪጠላ ድረስ ለአንድ ሙስሊም የተሟላ ኢማን እንደማይረጋገጥ ገለፁ። በሙስሊም ወንድሙ ላይ የዲን ጉድለት ከተመለከተም ለማስተካከል ይታገላል። በርሱ ላይ መልካምን ከተመለከተም ያበረታዋል፣ ያግዘዋል፣ የዲኑን ወይም የዱንያውን ጉዳይም ይመክረዋል።