explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲሸጥ ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ለሆነ ሁሉ የአሏህን እዝነት እንዲያገኝ ዱዓእ አደረጉለት፤ ይህም ዋጋውን በማናር ገዥን አያጨናንቅም፤ ይልቁን በመልካም ምግባር ይዋዋለዋል። ሲገዛም ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ስለሆነ እቃውን በማሳነስና በማጣጣል ዋጋውን አያራክስም። ያበደረውን እዳ ሲያስመልስም ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ስለሆነ ገንዘቡ እጅግ ያስፈለገውን ድሀ አያካብድበትም፤ ይልቁንም በእዝነትና ርህራሄ ይጠይቃል፤ ለተጨናነቀም የጊዜ ፋታ ይሰጣል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በሰዎች መካከል ያለን መስተጋብር ማስተካከል ሸሪዓው ከሚፈልጋቸው ዋንኛ ተፈላጊ ጉዳዮች መካከል መሆኑን እንረዳለን።
  • በሽያጭና በግዥም ይሁን በሌላም መስክ ከሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር እጅግ ያማረውን ስነምግባር መላበስ የሚበረታታ መሆኑን እንረዳለን።