ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች መካከል ኢማኑ የሞላው ስነምግባሩ ያማረ ሰው እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ለሰዎች ፊቱን ፈታ በማድረግ፣ መልካምን በመስጠት፣ ንግግርን በማሳመርና ሰዎችን ከማወክ በመቆጠብ ነው። ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ለምሳሌ ለሚስቱ፣ ለሴት ልጆቹ፣ ለእህቶቹና ለቅርብ ዘመዶቹ ምርጥ የሆኑ ናቸው። ምክንያቱም ሴቶች በመልካም ስነምግባር ሊኗኗራቸው ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የተገቡ ስለሆኑ ነው።