ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኝ ሁሉም ሙስሊም ላይ የሚሸከመውና የሚጠብቀው ኃላፊነት እንዳለበት ተናገሩ። ኢማምና መሪ አላህ ባስጠበቃቸው ኃላፊነት እረኞች (ኃላፊዎች) ናቸው። የሚመራቸውንም ሸሪዓቸውን መጠበቅ፣ በነርሱ ላይ ግፈኛ ከሆነ አካል እነርሱን መጠበቅ፣ ጠላቶቻቸውን መታገልና ሐቃቸውን አለማጥፋት ይገባዋል። ወንድም ለቤተሰቡ ቀለብ በማሟላት፣ መልካም አኗኗር በማኖር፣ በማስተማርና ስርዓት በማስያዝ ላይ ኃላፊነት አለበት። ሴትም በባሏ ቤት ውስጥ ቤቱን ባማረ መልኩ በማስተናበርና ልጆቹን በማነፅ ላይ ኃላፊነት አለባት። ስለዚህም ትጠየቃለች። አገልጋይ ባሪያና ተቀጣሪም በአለቃው ገንዘብ ላይ በእጁ ያለውን የአለቃውን ገንዘብ በመጠበቅ፣ እርሱን በማገልገል ሀላፊ ነው። ስለዚህም ይጠየቃል። እያንዳንዱ ሰው አላህ በሰጠው ሀላፊነት ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። እያንዳንዱም ሰው ስለ ሀላፊነቱ ይጠየቃል።