explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካምን ከመፈፀም እንዳናሳንስ አነሳሱን። ከነዚህ መካከልም ከሙስሊም ጋር በሚገናኝ ወቅት በፈገግታ ፊትን መፍታት ይጠቀሳል። አንድ ሙስሊም ይህን በመፈፀሙ ምክንያት ሙስሊም ወንድሙን ማዝናናትና በውስጡ ደስታን መጨመር ስለሚያመጣ በዚህ ላይ ሊጥር ይገባል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በአማኞች መካከል መዋደድ፣ ሲገናኙ ፈገግ ማለትና ማበሰር ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
  • ሸሪዓ ለሙስሊሞች በሚጠቅምና ህብረታቸውን አንድ በሚያደርግ ነገር ሁሉ መምጣቱ የዚህ ሸሪዓን ምሉዕነትና ጠቅላይነት ያስረዳናል።
  • ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካም በመስራት ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
  • በሙስሊሞች መካከል አንድነትን ስለሚያረጋግጥ በሙስሊሞች ላይ ደስታን መጨመር ተወዳጅ መሆኑን እንረዳለን።