explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰዎች ጋር በመበዳደር የሚንቀሳቀስ ወይም በዱቤ የሚሸጥላቸው ስለሆነ ሰው ተናገሩ። ለሰዎች ያበደረውን ብድር ለሚቀበልለት ሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ "ተበዳሪ ዘንድ ስትሄድ እዳውን መክፈል ተስኖት ካገኘኸው እለፈው" ይህም የሚከፍልበትን ፋታ በመስጠት፣ እዳውን በመፈለግ ላይ ችክ ባለማለት ወይም ጥቂት ቢጎድልም ያለውን በመቀበል ሊሆን ይችላል። ይህንንም የሚያደርገው አሏህ የእርሱንም ወንጀል እንዲያልፍለትና ይቅር እንዲለው ከመከጀል አኳያ ነበር። በሞተም ጊዜ አሏህም ማረው፤ ወንጀሉንም ይቅር አለለት።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ከሰዎች ጋር ባለ መስተጋብር መልካሙን መዋል፣ ይቅር ማለትና ሰው ሲቸግረው ብድሩን ማለፍ አንድ ባርያ በቂያማ እለት ከሚድንባቸው ትላልቅ ሰበቦች መካከል እንደሆነ እንረዳለን።
  • ለፍጡራን በጎ መዋል፣ ለአሏህ ስራን ጥርት ማድረግና እዝነቱንም መከጀል ለወንጀል መሀርታን ከሚያስገኙ ሰበቦች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።