explain-icon

ትንታኔ

ከሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና አንዱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ የሚጠቅመውን ነገር እንዲጠቁሙት ፈለገ። እርሳቸውም እንዳይቆጣ አዘዙት። ይህም ማለት ወደቁጣ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን እንዲርቅ፣ የሚያስቆጣ ነገር በተከሰተ ጊዜም ነፍሱን እንዲቆጣጠር፣ በቁጣው ወደ መግደል፣ መማታት፣ ስድብና የመሳሰሉት ነገር እንዳይሻገር ማለት ነው። ሰውዬውም በተደጋጋሚ ምክር እንዲጨምሩለት ፈለገ። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "አትቆጣ!" ከምትለው ምክር የዘለለ ምንም አልጨመሩለትም።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ቁጣ የክፋት መሰብሰቢያ ነውና ከቁጣና መንስኤዎቹ መጠንቀቅ እንደሚገባና ከሱ መጠበቅ የመልካም መሰብሰቢያ እንደሆነ እንረዳለን።
  • የአላህ ክልከላዎች ሲደፈሩ መቆጣትን የመሰለ ለአላህ ብሎ መቆጣት ምስጉን የሆነ ቁጣ ነው።
  • ሰሚው እስኪሸመድደውና አንገብጋቢነቱን እስኪገነዘብ ድረስ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ንግግርን መደጋገም እንደሚገባ እንረዳለን።
  • አዋቂ ከሆነ ሰው ምክር መፈለግ ያለውን ትሩፋት ተረድተናል።