ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ብርቱ የሚባለው ታግሎ ያሸነፈ ሳይሆን በቁጣ ወቅት እራሱን የተቆጣጠረ ነው።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።