ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሆነ ነገር ሲወድቅ የሚሰማውን አይነት አስደንጋጭ ድምፅ ሰሙ። እርሳቸው ዘንድ ያሉትንም ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ስለዚህ ድምፅ ምንነት ጠየቋቸው። ሶሐቦቹም "አላህና መልክተኛው አዋቂዎች ናቸው።" አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: ይህ የሰማችሁት ድምፅ ከሰባ አመት ጀምሮ ከጀሀነም ጫፍ የተወረወረ ድንጋይ ነው። ድምፁን በሰማችሁበት ጊዜ ወደ መጨረሻ ጥልቀቷ እስከደረሰበት የዛሬዋ ቀን ድረስ እየወረደና እየተምዘገዘገ ነበር።