ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል። እንዲህም ይላል 'ማን ነው የሚለምነኝ የምመልስለት? ማን ነው የሚጠይቀኝ ለርሱ የምሰጠው? ማን ነው ምህረትን ከኔ የሚፈልገው ለርሱ የምምረው?'" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።