ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሐዲሠል ቁድስ አላህ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ: ከወዳጆቼ መካከል አንድን የኔን ወዳጅ ያወከውና ያስቆጣው ከኔ ጋር ጠላት እንደሆነ አውጄያለሁም አሳውቄዋለሁም፤ "ወሊይ" (የአላህ ወዳጅ) የሚባለው: አላህን ፈሪ አማኝ ነው። አንድ ባሪያ ባለው ኢማንና አላህን ፈሪነት ልክ የአላህ ወዳጅነት ይኖረዋል። አንድ ሙስሊም አላህ ግዴታ ያደረገበትነን ትእዛዛትን መፈፀምና ክልክሎችን መተው ወደ አላህ እንደሚያቃርበው ምንም ነገር ወደ ጌታው ተወዳጅ በሆነ ነገር አይቃረብም። አንድ ሙስሊም ወደ ጌታው ከግዴታዎች ጋር በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የአላህን ውዴታ የሚያገኝ ቢሆን እንጂ፤ አላህ የወደደው ጊዜ በነዚህ አራት አካላቱ ላይ ለርሱ አጋዥ ይሆነዋል። በመስሚያው ያግዘዋል። አላህን ከሚያስደስት ነገር ውጪ ሌላ ምንም አይሰማም። በመመልከቻው ያግዘዋል። አሏህ እንዲታይ የሚወደውንና የሚያስደስተውን ነገር እንጂ ሌላ አይመለከትም። በእጁም ያግዘዋል። በእጁ አላህን ከሚያስደስት ነገር በቀር አይሰራም። በእግሩም ያግዘዋል። አላህን ወደሚያስደስት ነገር ካልሆነ በቀር አይራመድም። መልካም ነገር ወዳለበት ካልሆነ በቀር አይሮጥም። ከዚህም ጋር አላህን አንዳች ነገር ከጠየቀው አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፤ ተማፅኖውንም የሚሰማው ይሆናል። በአላህ ጥበቃን ካስፈለገውና የአሏህን ከለላ ፈልጎ ከተጠጋ ጥራት የተገባው አላህም ከሚፈራው ነገር ይጠብቀዋል። ቀጥሎም አላህ እንዲህ አለ: የሙእሚንን ነፍስ ስወስድ ለርሱ በማዘን እንደማመነታው እኔ ከምሰራው በአንዳችም ነገር አላመነታሁም። ምክንያቱም እርሱ ካለው ህመም አንፃር ሞትን ይጠላል። አላህ ደግሞ ሙእሚንን የሚያሳምም ነገር ይጠላል።