ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሐዲሠል ቁድስ ውስጥ አላህ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ: የአደም ልጅ ሆይ! እኔን በመለመን፣ እዝነቴን በመከጀልና ተስፋ ባለመቁረጥ ላይ እስከዘወተርክ ድረስ ይህ ወንጀልህና ሀጢዐትህ ከትላልቅ ወንጀሎች ቢሆንም እንኳ እሸሽገዋለሁ፣ ምንም ሳይመስለኝም አብሰዋለሁ። የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀልህ በሰማይና በምድር መካከል ያለውን በሚሞላና ምድርንም ከጫፍ እስከጫፍ በሚደርስና ጎኖቿን በሚያጠቃልል መልኩ ቢበዛ ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ ብዛቱ ምንም ሳይመስለኝ ሁሉንም ላንተ አብሰዋለሁም እምርሃለሁኝም። የአደም ልጅ ሆይ! አንተ ከሞት በኋላ ወደኔ ምድርን በሚሞላ ወንጀሎችና ሀጢዐቶች ብትመጣ በብቸኝነቴ አምልከኸኝ በኔ አንድንም ሳታጋራ ከሆነ የሞትከው እነዚህን ወንጀሎችህንና ሀጢዐቶችህን ምድርን በሚሞላ ምህረት እገናኛቸዋለሁ። እኔ ምህረተ ሰፊ ነኝና። ከሺርክ በስተቀርም ሁሉንም ወንጀሎችህን እምራለሁ።