ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ማዒዝ ቢን ማሊክ አልአስለሚይን ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዝሙት ቅጣት በድንጋይ ወግረው ከገደሉት በኋላ ተነሱና ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ: አላህ የከለከላቸው የሆኑትን እነዚህን ቆሻሻ፣ ፀያፍና አስቀያሚ ወንጀሎች ራቁ። ከነዚህ ወንጀሎች አንዳችን የፈፀመ ካለም ሁለት ነገር መፈፀም ይጠበቅበታል: የመጀመሪያው: አላህ ወንጀሉን እንደሸሸገለት ተሸሽጎ ወንጀሉን አለመናገር። ሁለተኛው: ወደ አላህ ተውበት በማድረግ መቻኮል፣ በርሱ ላይ አለመዘውተር ነው። ወንጀሉ ለኛ ግልፅ የሆነችበት ሰው በርሱ ላይ በአላህ መጽሐፍ መሰረት ለዚህች ወንጀሉ የተጠቀሰውን ቅጣት እንፈፅምበታለን።