ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ከባሮቹ ንስሀቸውን እንደሚቀበል ተናገሩ። አንድ ባሪያ በቀን ወንጀል ሰርቶ በምሽት ንስሀ ከገባም አላህ ንስሀውን ይቀበለዋል። በምሽት ወንጀል ሰርቶ በቀን ንስሀ ከገባም አላህ ንስሀውን ይቀበለዋል። አሏህ ንስሀ ለሚገቡ ሰዎች እጁን የሚዘረጋውም በንስሀቸው ስለሚደሰትና ንስሀቸውንም ለመቀበል ነው። የዚህ አለም ፍፃሜን የምታሳውቀው የፀሀይ ከመግቢያዋ በኩል መውጣት እስኪከሰት ድረስም የንስሀ በር ክፍት ከመሆን አይወገድም። ፀሀይ በመግቢያዋ በኩል የወጣች ጊዜ ግን የንስሀ በር ይዘጋል።