ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከወንጀሉ ወደ አላህ በመመለስ ኒያ ቁሞ ሁለት ረከዓ ሰግዶ ከዚያም አላህን ምህረት የሚጠይቅ አንድም ኃጢዓት የሚሰራ ባሪያ እንደሌለ ተናገሩ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን የአላህ ቃል አነበቡ: {ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢዐቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ከአላህም ሌላ ኀጢዐቶችን የሚምር አንድም የለ። (በስህተት) በሰሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት (ተደግሳለች)።} [ኣሊ ዒምራን:135]