ዑባዳ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ትልቁን የበድር ዘመቻ ከተሳተፉት ሶሐቦች መካከል አንዱ ነበር። መልክተኛው በመካ ሳሉ ወደ መዲና ከመሰደዳቸው በፊት ሚና በተደረገው የዓቀባው ምሽት የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለመርዳት እርሳቸውን ቃልኪዳን ለመጋባት ከመዲና ከመጡ የህዝቦቹ መሪዎች መካከል አንዱ ልዑክ ነበር። የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በባልደረቦቻቸው መካከል ተቀምጠው ሳለ ባልደረቦቻቸውን በነዚህ ጉዳዮች ቃልኪዳን እንዲጋቧቸው ፈለጉ። አንደኛ: አላህን በማምለክ ላይ ቅንጣት ታክል ላያጋሩ፤ ሁለተኛ: ላይሰርቁ፤ ሶስተኛ: ፀያፉን የዝሙት ተግባር ላይፈፅሙ፤ አራተኛ: ወንዶች ልጆቻቸውን ድህነትን ፍራቻ ወይም ሴት ልጆቻቸውን ውርደት ፍራቻ እንዳይገድሏቸው፤ አምስተኛ: በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው መካከል የሚፈጥሩትን ውሸት እንዳይፈፅሙ፤ ይህም ምንም እንኳ የተቀሩት አካላቶች ቢሳተፉም አብዛኛው ተግባራት የሚፈፀሙት በሁለቱ ስለሆነ ነው። ስድስተኛ: ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመልካም ትእዛዛቸው እንዳያምፁ ነው። ከነርሱ መካከል በዚሁ ቃልኪዳን ላይ የፀናና የዘወተረ ምንዳው አላህ ዘንድ ነው። ከተጠቀሱት ወንጀሎች መካከል ከሽርክ ውጪ የሆኑትን አንዳቸውንም የሰራና ለስራውም ዱንያ ላይ አላህ ባስቀመጠው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ የተቀጣ ሰው ይህ ቅጣት ለርሱ ወንጀሉን ማስማሪያ ማካካሻ ይሆንለታል። ከነዚህ ወንጀሎች መካከል አንዳችን ሰርቶ ከዚያም አላህ የሸሸገለት ሰው የርሱ ጉዳይ የሚመለሰው ወደ አላህ ነው። ከፈለገ ይቅር ይለዋል። ከፈለገም ይቀጣዋል። በቦታው ያሉት ሁሉም ሶሐቦችም በዚህ ላይ ቃል ተጋቧቸው።