ዑቅባህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙእሚን በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ስለሚድንባቸው ሰበቦች ጠየቀ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሶስት ነገሮች ላይ አደራ አሉት። የመጀመሪያው: ምንም መልካምነት ከሌለው ነገርና መጥፎ የተባለን ንግግር ሁሉ ከመናገር ምላስህን ቆጥብ! ከመልካም በቀር ምንም አትናገር። ሁለተኛው: አላህን ለብቻህ ለማምለክ ቤትህ አዘውትር! አላህን በማምለክ ተጠመድ! ከፈተናዎች በቤትህ ተከለል። ሶስተኛው: ከሰራኸው ወንጀል ተመለስ፣ ተፀፀት፣ አልቅስ!