አንድ ፀጉሩ የተበታተነ፣ ድምፁ ከፍ ያለ፣ የሚናገረው የማይገባ የነጅድ ነዋሪ የሆነ ሰው ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣ። ወደነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀረበና ስለ እስልምና ግዴታዎችም ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሶላት ጀመሩና አላህ በሁሉም ቀንና ምሽቶች አምስት ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገበት ነገሩት። እርሱም: ከነዚህ አምስት ሶላቶች በቀር ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ? አላቸው። እርሳቸውም: ሱና ሶላቶችን በፈቃደኝነት ልትሰግድ ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም አሉት። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው እንዲህ አሉት: በአንተ ላይ አላህ ግዴታ ካደረገብህ ነገሮች መካከል የረመዳንን ወር መጾም አንዱ ነው። ሰውዬውም "ከረመዳን ጾም ውጪ ሌላ ጾም መጾም ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ?" አላቸው። እርሳቸውም: በፈቃደኝነት ካልጾምክ በቀር የለብህም አሉት። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘካን አወሱለት። ሰውዬውም: የግዴታ ዘካዬን ካወጣሁ በኋላ ሌላ ምፅዋት ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ? አላቸው። እርሳቸውም: በፈቃደኝነት ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም አሉት። ሰውዬው እነዚህን ግዴታዎች ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰማ በኋላ ከእነሱ ምንም ሳይጨምርና ሳይቀንስ ዘውትሮ እንደሚተገብር በአላህ ምሎ እየተናገረ ዞሮ ሄደ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ይስፈንና ይህን አስከትለው ሰውዬው የማለበትን ነገር የእውነት ከፈፀመ ከሚድኑት ሰዎች ይሆናል አሉ።