ሚቅዳድ ቢን አስወድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና -ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጦርነት ላይ ከአንድ ከሀዲ ሰው ጋር ቢገናኝና በሰይፍ ብቻ ለብቻ ቢጋጠሙ ከሀዲውም አንድ እጁን በሰይፍ አግኝቶ ከቆረጠ በኃላ ከርሱ ሸሽቶ በዛፍ ቢመሸግና "ላኢላሃ ኢለሏህ" ቢል እጄን ከቆረጠ በኋላ እርሱን መግደል ይፈቀድልኛልን? በማለት ጠየቀ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዳትገድለው! አሉት። እርሱም: የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሱ’ኮ አንድ እጄን ቆርጧል። ይህን ከማድረጉም ጋር አልገድለውምን? አላቸው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: እንዳትገድለው! እርሱ ደሙን ማፍሰስ ከተከለከሉት ሆኗል። ከሰለመ በኋላ ከገደልከው እርሱ በእስልምናው ደሙ የተጠበቀ ስለሆነ ባንተ ደረጃ ይሆንና አንተ ደሞ እርሱን በመግደልህ በቂሷስ ህግ መሰረት ደምህ መፍሰሱ የተፈቀደ ስለምትሆን በርሱ ደረጃ ላይ ትሆናለህ! አሉት።