ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከለከለውን ሀሜት ምንነት : ሙስሊምን በሌለበት በሚጠላው ነገር ማውሳት መሆኑን በመግለፅ አብራሩ። ይህም ተፈጥሯዊውም ሆነ ስነ ምግባሪያዊ ባህሪውን ቢያወሳ ተመሳሳይ ነው። እውሩ ፣ አጭበርባሪ ፣ ውሸታምና የመሳሰሉትን እሱ ላይ የሚገኙ የተወገዙ መገለጫዎችን በማውሳት ማማት ማለት ነው። የተወሱት እሱ ላይ የሌሉ ባህሪያት ከሆኑ ግን ከሀሜትም የባሰ ነው። እሱም መቅጠፍ (ቡህታን) ነው የሚሆነው :- ማለትም በሰው ላይ የሌሉበትን ባህሪያት መቅጠፍ ነው።