ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እውነተኛ ሆኖም ቢሆን በመሸጥና በመግዛት ወቅት ከመማልና መሃላን ከማብዛት አስጠነቀቁ። መሀላ ሸቀጡና እቃው እንዲፈለግ ምክንያት እንደሆነ ነገር ግን የትርፉና የስራውን በረከት የሚያጎልና የሚያጠፋ መሆኑንም ተናገሩ። አላህ በርሱ ላይ የመሰረቅ ወይም የመቃጠል ወይም የመስመጥ ወይም የመዘረፍ ወይም የመነጠቅ ወይም ከዚህ ውጪ ያሉ ገንዘቡ እንዲጠፋ የሚያደርጉ ምክንያቶችን ሊጋርጥበት ይችላል።