ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አጎታቸው አቡጧሊብ ዘንድ ጣእረሞት ላይ ሳለ ገቡና እንዲህ አሉት: አጎቴ ሆይ! በርሷ ምክንያት አላህ ዘንድ የምመሰክርልህን ቃል "ላኢላሃ ኢለሏህ" በል። አቡጀህልና ዐብደላህ ቢን አቢኡመያህም "አቡጧሊብ ሆይ! የአባትህ የዐብዱልሙጦሊብን መንገድ ትተዋለህን?!" አሉ። የጣኦት አምልኮዋቸውን ለማለት ነው። አቡጧሊብ በመጨረሻ ንግግራቸው ላይ "በዐብዱል ሙጦሊብ መንገድ ላይ ነኝ!" እስኪሉ ድረስም ይህን ከመጎትጎት አልተወገዱም። ይህም የሺርክና የጣኦት አምልኮ መንገድ ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ጌታዬ እስካልከለኝ ድረስ ምህረትን እለምንልሃለሁ።" አሉ። ይህ የአላህ ንግግርም ወረደ: {ለነቢዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ እነሱ (ከሀዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ምህረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም።} [አት-ተውባህ: 113] በአቡ ጧሊብ ዙሪያም ይህ የአላህ ንግግር ወረደ: {አንተ የወደድከውን ሰው ፈፅሞ አታቀናም። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል። እርሱም ቅኖቹን አዋቂ ነው።} [አልቀሶስ: 56]" አንተ መቃናቱን የወደድከውን ሰው አታቀናም። በአንተ ላይ ያለው ግዴታ ማድረስ ብቻ ነው። አላህ የሻውን ያቀናል።