አነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ሲሉ ተናገሩ: በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህ የአላህ ቃል የወረደ ጊዜ: {(1) እኛ ላንተ ግልፅ የሆነን መክፈት ከፈትንልህ። (2) አላህ ከኀጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ)። (3) አላህ ብርቱን እርዳታ ሊረዳህም (ከፈተልህ)። (4) እርሱ ያ በምእመናን ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው። ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት። አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው። (5) ምእመናንንና ምእመናትን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈስባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ሊያገባቸው ከነርሱም ሀጢአቶቻቸውን ሊያብስላቸው (በትግል አዘዛቸው)። ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ ማግኘት ነው።} [አልፈትሕ: 1-5] እነዚህ አንቀጾች የወረዱትም ሶሓቦች በሑደይቢያ ስምምነቱ መካሄድ ምክንያት ዑምራን ከማድረግ ክልከላ ተጥሎባቸው ሀድያቸውን (ቁርባናቸውን) በሑደይቢያ አርደው ስምምነቱ የሙስሊሞችን ጥቅም ያስጠበቀ አይደለም በሚል ሀዘንና ትካዜ ወርሯቸው ከዛ በሚመለሱበት ወቅት ነበር። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: እኔ ዘንድ ከዱንያ ባጠቃላይ ተወዳጅ የሆነች አንቀፅ በኔ ላይ ወረደች። ቀጥለውም አነበቧት።