ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሙስሊም በህብረት የሰገደ ጊዜ ይህቺ ሶላቱ ቤቱ ውስጥ ወይም ሱቁ ውስጥ ከሚሰግደው ሰላት ሀያ ምናምን እጥፍ የምትበልጥ መሆኗን ተናገሩ። ቀጥለውም የዚህን ምክንያት ተናገሩ። እርሱም ሰዉዬው ዉዱእን አሟልቶና አሳምሮ አድርጎ ከዚያም ሶላትን ብቻ ፈልጎ ወደ መስጊድ እስከወጣ ድረስ በእያንዳንዷ እርምጃው ምክንያት ደረጃው ከፍ ይላል፤ ወንጀሉም ይታበስለታል። መስጂድ ገብቶም ሶላትን እየጠበቀ ከተቀመጠ ሶላትን እስከተጠባበቀበት ጊዜ ድረስ የሶላትን ምንዳና አጅር ያገኛል። መላእክቶችም የሰገደበት ስፍራ ላይ እስከተቀመጠ ድረስ ለርሱ እንዲህ እያሉ ዱዓ ያደርጉለታል፦ "አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው" ይህ ግን ዉዱኡን እስካላበላሸ ወይም ሰዎችን ወይም መላእክትን የሚያውክ ነገር እስካልፈፀመ ድረስ ነው።