ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ቀን ፈጅርን አሰገዱና ቀጥለው እከሌ ይህ ሶላታችን ላይ ተሳትፏልን? ብለው ጠየቁ። ሶሐቦችም "አይ" አሉ። ቀጥለውም ሌላን ሰው "እከሌስ ተሳትፏልን?" አሉ። ሶሐቦችም "አይ" አሉ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: የፈጅርና የዒሻ ሶላቶች በነርሱ ወቅት ድካም ስለሚበዛና በጨለማ ስለማይታዩ ይዩልኝን ማግኘት የሚያንስበት ወቅት ስለሆነ በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባድ ሶላቶች ናቸው። እናንተ አማኞች ሆይ! በሱብሒና በዒሻ ሶላቶች የሚገኘውን ተጨማሪ ምንዳና አጅር ብታውቁ ኖሮ (ምንዳ የሚገኘው እንደ አድካሚነቱ ልክ ነውና።) በእጃችሁና በጉልበታችሁ እየተጎተታችሁና እየዳኸችሁ ትመጡ ነበር። የመጀመሪያው ሰልፍ ከኢማሙ ጋር ያላቸው ቀረቤታ ልክ የመላእክቶች ሰልፍ ወደ አላህ እንዳላቸው ቀረቤታ ነው። አማኞች በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ትሩፋት ቢያውቁ ኖሮ ወደርሱ ይሽቀዳደሙ ነበር። ሰውዬው ከአንድ ሰው ጋር የሚሰግደው ሶላት ለብቻው ከሚሰግደው ሶላት የበለጠ ምንዳና አጅር ያስገኝለታል። ከሁለት ሰዎች ጋር የሚሰግደው ሶላት ደሞ ከአንድ ሰው ጋር ከሚሰግደው ሶላት የበለጠ ምንዳና አጅር ያስገኝለታል። ሰጋጆች የበዙበት ሶላት ወደ አላህ እጅግ ተወዳጅና በላጭ የሆነ ሶላት ነው።