ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰውዬው ከኢማም ጋር በህብረት የሚሰግደው ሶላት ምንዳና አጅሩ ቤቱ ወይም ሱቁ ውስጥ ብቻውን ከሚሰግደው ሃያ አምስት ሶላት እንደሚበልጥ ገለፁ። ቀጥለው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የምሽትና የቀን መልዐክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት እንደሚሰባሰቡ አወሱ። ቀጥሎም አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ ይህንን ለማመሳከር እንዲህ አለ: ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ: {የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78] ማለትም: የፈጅር ሶላት የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች የሚገኙበት ነው ማለት ነው።