ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶላት ላይ ለወንዶች ምርጡ፣ በርካታ ምንዳንና ደረጃን የሚያስገኘው ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ወደ ኢማሙ ስለቀረቡ፣ የርሱን ቁርአን ስለሚሰሙና ከሴቶችም ስለራቁ ነው። መጥፎው፣ ጥቂት ምንዳና ደረጃ የሚያገኘው፣ ከሸሪዓ ዓላማ የሚርቀው ሰልፍ ደግሞ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። የሴቶች ምርጥ ሰልፍ ደግሞ የመጨረሻው ሰልፍ እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ለነሱ ሸሸግ የሚያደርጋቸው፣ ከወንዶች ጋር ከመቀላቀል፣ በነርሱ ከመታየት፣ በነርሱ ከመፈተንም የራቀ ስለሆነ ነው። መጥፎው ሰልፍ ደግሞ ከወንዶች ስለሚቀርብ፣ ለፈተና ስለምትጋለጥ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው።