ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።