ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሣቢት ቢን ቀይስን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አጡትና ስለርሱ ጠየቁ። አንድ ሰውዬም "የጠፋበትን ምክንያት ለርሶ መረጃውን አገኝሎታለሁ።" በማለት ወደርሱ ሄደ። ቤቱ ውስጥ አዝኖ አንገቱን አቀርቅሮ አገኘው። "ምን ሆነህ ነው?" ብሎ ጠየቀው። ሣቢትም ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ድምፅ በላይ ድምፁን ከፍ ያደርግ እንደነበር፤ አላህም ይህንን ያደረገ ሰው ስራው እንደተበላሸና የእሳት ባለቤት እንደሆነ በመናገሩ በርሱ ላይ የደረሰውን መጥፎ ነገር ነገረው። ሰውዬውም ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመመለስ ይህንን ነገራቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰውዬውን ወደ ሣቢት ተመልሶ ከእሳት ሰዎች እንዳልሆነ ነገር ግን ከጀነት ሰዎች እንደሆነ እንዲያበስረው አዘዙት። ይህም የሆነው የርሱ ድምፅ ከፍ ያለ መሆኑ ተፈጥሯዊ እና የነቢዩም የአንሷሮችም ኹጥባ አድራጊም ስለነበር ነው።