ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመዲና ነዋሪ የሆኑትን አንሷሮች መውደድ የኢማን መሙላት ምልክት መሆኑን ተናገሩ። ይህም የሆነው ኢስላምንና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመርዳት ላይ፣ ሙስሊሞችን በማስጠጋት ላይ ባደረጉት ልፋት፣ ገንዘቦቻቸውንና ነፍሳቸውንም በመለገስ በኩል ቀዳሚ ስለሆኑ ነው። እነርሱን መጥላትም የንፍቅና ምልክት ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንሷሮችን የወደደ አላህ እንደሚወደው እነሱን የጠላም አላህ እንደሚጠላው ገለፁ።