ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነገ በመዲና አቅራቢያ በምትገኘው የኸይበር ከተማ አይሁዶች ላይ ሙስሊሞች ድልን እንደሚያገኙ ለሶሐቦች ተናገሩ። ይህም ባንዲራውን በሚሰጡት ሰው እጅ ነው። ባንዲራ ማለት ለመታወቂያነት ሰራዊቱ የሚይዘው ምልክት ነው። ይህ ሰው ከባህሪዎቹ መካከል አላህና መልክተኛውን ይወዳል፤ አላህና መልክተኛውም ይወዱታል። ዑመር ቢን አልኸጣብም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከዛ ቀን በቀር ሹመትን እንዳልወደዱና አላማ አድርገው እንዳልያዙ አወሱ። ይህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህና መልክተኛውን ይወዳል ብለው ያወሱትን መገለጫ ለማግኘት በመከጀል ነው። ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አይተውት እንዲጠሩት ይህንንም ባንዲራ ለመያዝ በመጓጓትና በመከጀል ተንጠራሩ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጠርተው ባንዲራውን ሰጡት። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰራዊቱን ይዞ እንዲንቀሳቀስ፤ ጠላቶቹን ከተገናኘ በኋላም ምሽጎቹን በድልና በማሸነፍ አላህ እስኪከፍትለት ድረስ በእረፍትም ይሁን ወይ በማቆም አለበለዚያም በስምምነት ምክንያት ጦርነቱን እንዳያቆም አዘዙት። ዐሊይም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድላቸውና - ተጓዙ ከዚያም የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትእዛዝ ላለመፃረር ሳይዞሩ ቆም ብለው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎቹን በምን ላይ ነው የምዋጋቸው?" አሉ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን እስኪመሰክሩ ተዋጋቸው። ይህን ተቀብለው ወደ እስልምና ከገቡ ደምና ገንዘባቸውን ከአንተ ተከላክለዋል። በአንተም ላይ እርም ተደርጓል። በሐቁ ካልሆነ በቀር ማለትም በእስልምና ህግጋት መሰረት በርሱ ሊገደሉበት የሚገባቸውን ወንጀል ወይም ግድያ እስካልፈፀሙ ድረስ እንዳትገድላቸው ማለት ነው። ሒሳባቸው ታዲያ አላህ ዘንድ ነው።