ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በአንድ ዘመን ከሚኖሩ ማህበረሰቦችና ትውልዶች መካከል ምርጡ ማህበረሰብና ትውልድ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እና ሶሐቦች የነበሩበት ማህበረሰብና ትውልድ መሆኑን ተናገሩ። ቀጥሎ ደግሞ ከዛ ቀጥለው የመጡ የአላህን መልክተኛ ሳያገኙ ሶሓቦችን ያገኙ አማኞች መሆናቸውን ተናገሩ። ቀጥሎ ደግሞ ከዛ ቀጥለው የመጡ አትባዑ ታቢዒኖች ናቸው። ይህን ሐዲሥ የተናገረው ሶሓባ አራተኛው ትውልድ በመጠቀሱ ዙሪያ አመንትቷል። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ከነዚህ በኋላ ሰው የማይተማመንባቸው ከዳተኞች የሆኑ፤ ለምስክርነት ሳይጠየቁ በፊት ምስክርነትን የሚሰጡ፤ ስለት ተስለው ስለታቸውን የማይሞሉ፤ ውፍረት በግልፅ እስኪስተዋልባቸው ድረስ መብላትና መጠጣት የሚያበዙ ሰዎች ይመጣሉ።" አሉ።