ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦችን ልቦች በርሷ ምክንያት የራዱበትና ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰ ምክር መከሩ። ሰሐቦችም የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምክራቸው ጥግ የደረሰ መሆኑን ስላዩ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምክሮት የተሰናባች ምክር ትመስላለች።" በማለት ከርሳቸው ህልፈት በኋላ አጥብቀው የሚይዙትን አደራ ጠየቁ። እርሳቸውም "አላህን በመፍራት አደራ እላቹኃለሁ።" አሉ። ይህም ግዴታዎችን በመፈፀምና ክልክሎችን በመተው ነው። "ባሪያ በናንተ ላይ ቢሾም ወይም መሪ ሆኖ ቢመጣባችሁ እንኳ ለመሪዎች መስማትና መታዘዝን አደራ እላችኃለሁ።" ማለትም በናንተ ላይ ደረጃው የወረደ (አርጋችሁ የምታስቡት) ፍጡር መሪ ቢሆን እንኳ ፈተና ይቀጣጠላል ተብሎ ስለሚሰጋ በዚህ ላይ እምቢተኛ አትሁኑ ታዘዙት ማለት ነው። "እነሆ ከናንተ መካከል የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ያያል።" ቀጥለውም ከዚህ ልዩነት መውጫውን ገለፁላቸው። እሱም የርሳቸውን ሱና(ፈለግ) እና ከርሳቸው በኋላ የተመሩ የሆኑት ቅን ምትኮቻቸውን ሱና አጥብቆ በመያዝ ነው። እነሱም: አቡ በከር አስሲዲቅ፣ ዑመር ቢን አልኸጧብ፣ ዑሥማን ቢን ዐፋንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ የሁሉንም መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ናቸው። አጥብቃችሁ የምትይዙትም በማኘኪያ ጥርስ ነክሶ እንደመያዝ ነው። በዚህም ለማለት የፈለጉት ሱናን በመያዝና በማጥበቅ ላይ መጠንከርን ለመጠቆም ነው። በሃይማኖት ውስጥ ከተፈበረኩ አዳዲስ መጤ ጉዳዮችም አስጠነቀቋቸው። ሁሉም አዲስ መጤ ነገር ጥመት ነውና።