ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኛ ላይ መሪዎች እንደሚሾሙና ከፊል ስራዎቻቸው ከሸሪዓ ጋር የተስማማ ስለሆነ መልካም እንደምንለውና፤ ከፊሉን ደግሞ ከሸሪዓ ጋር ስለሚፃረር እንደምናወግዘው ተናገሩ። ውግዝ ተግባሮቻቸውን ማውገዝ ያልቻለና በቀልቡ የጠላ ሰው በርግጥም ከወንጀልና ንፍቅና ጠራ። በእጁ ወይም በአንደበቱ ማውገዝ የቻለ ሰውና በነርሱ ላይ ይህንን ያወገዘ በርግጥ ከወንጀልና ከወንጀል ተባባሪነት ሰላም ሆኗል። ነገር ግን ድርጊታቸውን የወደደና በርሱ ላይ የተከተላቸው እነርሱ እንደጠፉት ይጠፋል። ከዚያም ሶሐቦች ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይህን አይነት ባህሪ የተላበሱ መሪዎችን አንዋጋምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "በመካከላችሁ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም እንዳትዋጓቸው!" በማለት ከዚህ ከለከሏቸው።