ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመሪዎች ትእዛዝ አምፆ በመውጣት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከተስማሙበት መሪ ያፈነገጠ ሰው በዚህ ያለመታዘዝና አማፂነት ሁኔታ ላይ ሆኖ ቢሞት የእነዚያ መሪን የማይታዘዙ፣ ወደ አንድ ህብረት የማይጠጉ በተቃራኒ ቡድንተኛና ወገንተኛ ሁነው ከፊሉ ከፊሉን ይዋጉ የነበሩት የድንቁርና ዘመን ባለቤቶችን አይነት አሟሟት ሙቷል አሉ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እውነተኛው ከውሸተኛው ባልተለየበት ባንዲራ ስር የተዋጋ ሰው ቁጣውና እምነቱ ሐቅን ለመርዳት ሳይሆን ለጠራ ህዝባዊ ወይም ጎሳዊ ወገንተኝነት የሆነ ፤ ያለእውቀትና እርግጠኝነት ለወገንተኝነት የሚዋጋ ሰው በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ከተገደለ ሞቱ እንደ ድንቁርና ዘመን ሞት ነው የሚሆነው ብለው ተናገሩ። በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኡመት ላይ ለመሪነት የወጣ መልካሙንም መጥፎውንም የሚማታ፣ በሚፈፅመው ድርጊት ላይ ደንታ የሌለው፣ አማኞችን በመግደል የሚደርስበትን ቅጣት የማይፈራ፤ ከከሀዲያንና ከመሪዎች ጋር ያለውን ቃል ኪዳን ከመጠበቅ ይልቅ ቃል ኪዳኑን የሚያፈርስ (ይህ ትልቅ ወንጀለም ነው።) ይህን የሰራ ሰው ለዚህ ትልቅ ዛቻ የተገባ ይሆናል።