ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሶሐቦች ጋር ለመሪዎችና አስተዳዳሪዎች በገርም ይሁን በከባድ፣ በሀብትም ይሁን በድህነት ወቅት፣ ትእዛዞቻቸው ነፍስ የምትወደውም ሆነ የምትጠላው ለነርሱ ታዛዥ እንዲሆኑ ቃል ኪዳን ፈፀሙ። መሪዎች በህዝብ አጠቃላይ ገንዘብ ወይም በማእረግ ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች አድሎ ቢፈፅሙ እንኳ መሪዎችን በመልካም መታዘዝና መስማት ግዴታ መሆኑንና እነርሱንም አምፀው ላይወጡ ቃል ኪዳን ፈፀሙ። ምክንያቱም መሪዎችን በመዋጋት የሚመጣው ፈተናና ብልሽት በግፋቸው ሳቢያ ከሚከሰተው ብልሽት እጅግ የገዘፈ ነውና። በንግግራቸው ለአላህ ብቻ ያጠሩ (ሙኽሊስ) ሲሆኑና ወቃሻቸውን ሳይፈሩ እውነትን በማንኛውም ስፍራ መናገርም ሌላው ቃል ኪዳን የተጋቡት ጉዳይ ነው።