ከመዕቂል ቢን የሳር አልሙዘኒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: እኔ የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

እያንዳንዱ አላህ በሰዎች ላይ ተጠያቂና ሀላፊ ያደረገው ሁሉ እንደመሪነት ጠቅላይ ሀላፊነትን የሚያስተዳድርም ይሁን ወይም በቤቱ ሀላፊ እንደሆነ ወንድና በቤቷ ሀላፊ እንደሆነች ሴት ውስን ሀላፊነትም ይሁን የሀላፊነት ግዴታውን ካጓደለ፣ ቅን ሳይሆን ካጭበረበረና ዲናዊና ዓለማዊ ግዴታውን ካጠፋ ለከባድ ቅጣት እንደተገባ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ይህ ዛቻ በጠቅላይ መሪውና ሚኒስትሮቹ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን አላህ በሀላፊነት የሾመውን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።
  • በአንዳች የሙስሊሞች ጉዳይ ላይ የተሾመ ሰው ያለበት ግዴታ ለነሱ ቅን መሆን፣ አደራውን በመወጣት ላይ መታገልና ማጭበርበርን መጠንቀቅ ነው።
  • ጠቅላይም ይሁን ውስን፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሀላፊነት ላይ የተሾመ ሁሉ ተጠያቂነቱ ትልቅ መሆኑን እንረዳለን።