ከዐርፈጀህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ: "ጉዳያችሁ በአንድ መሪ የተሰበሰበ ሁኖ ሳለ አንድነታችሁን ሊሰነጥቅ ወይም ህብረታችሁን ሊበታትን የመጣ ሰውን ግደሉት።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።