ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ከሶላት ከማሰላመታቸው በፊት ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቁ ነበር። እኛንም በአላህ ከነርሱ እንድንጠበቅ አዘዙን። የመጀመሪያው: ከቀብር ቅጣት ነው። ሁለተኛው: የትንሳኤ ቀን ከእሳት ቅጣት ነው። ሶስተኛው: ከህይወት ፈተናዎች ሲባል ክልክል ከሆኑ ዓለማዊ ዝንባሌዎችና አጥማሚ ማደናገሪያዎች፤ እንዲሁም በሞት ሰአት ከሚያጋጥሙ ፈተናዎች ሲባል ደግሞ በጣእረ ሞት ሰአት ከኢስላም ወይም ሱና መጥመምን የመሰሉ ወይም በሁለቱ መላእክት መጠየቅን ከመሰለ የቀብር ፈተና ማለት ነው። አራተኛ: በመጨረሻ ዘመን የሚወጣ ከሆነው ከመሲሕ ደጃል ፈተና ነው። አላህ በርሱ አማካኝነት ባሮቹን ይፈትናል። ዱዓው ላይ እርሱ ተለይቶ የተጠቀሰው የርሱ ፈተናና ማጥመሙ ከባድ ስለሆነ ነው።